Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዘመን ተሻጋሪ የስኬት ማህተም ነው – ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ማንኛውንም ነገር ማሳካት እንደምንችል በተግባር ያረጋገጠ ዘመን ተሻጋሪ የስኬት ማህተም ነው አሉ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ።

የግድቡን መጠናቀቅን በማስመልከት በጅግጅጋ ከተማ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት፥ ግድቡ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን በአንድነት ያስተባበረና ሀገራዊ መግባባትን ያጎለበተ ታላቅ ፕሮጀክት ነው።

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ኃይል ከማመንጨት ባሻገር ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን ተሰሚነት ከፍ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸው፥ የብልጽግና ጉዟችን እንዲሳካ ያደርጋል ነው ያሉት፡፡

ግድቡ የትውልድ አሻራ ያረፈበት የድል ሀውልት፣ የሕብረትና የእድገታችን መገለጫና የአዲሱ ትውልድ የተስፋ ጮራ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ ተጠናቅቆ ለምረቃ መብቃቱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ትልቅ ትርጉም እንዳለው ተናግረዋል፡፡

ግንባታው ከተጀመረበት ግዜ ጀምሮ በርካታ የውስጥና የውጪ ፈተናዎች ሲያጋጥሙ እንደነበር አስታውሰው፥ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ቆራጥ አመራር እና በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያልተቋረጠ ድጋፍ ለስኬት መብቃቱን አስረድተዋል።

ይህም እንደ ሕዝብ በአንድነት ስንቆም ታሪክ መስራት እንደምንችል ያሳየንበት ትልቅ ትውልድ ተሻጋሪ የልማት ትሩፋት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ከዚህም ባለፈ በራሳችን ገንዘብ የገነባነው በመሆኑ ለአንድ ዓላማ ስንተሳሰር ማንኛውንም ነገር ማሳካት እንደምንችል በተግባር ያረጋገጠ ዘመን ተሻጋሪ የስኬተ ማህተም ነው ብለዋል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋ ከተደረጉት ሜጋ ፕሮጀክቶች መካከል የተወሰኑት በሶማሌ ክልል የሚገነቡ መሆናቸውን ጠቅሰው፥ ይህም ለዘመናት ከልማት ርቆ ለኖረው የክልሉ ሕዝብ የአዲስ ዓመት ትልቅ ብስራት እንደሆነ አመልክተዋል፡፡

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version