አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በአፋር ክልል ሎጊያ ሰመራ ከተማ ለሚካሄደው 10ኛው የኢትዮጵያ የከተሞች ፎረም የዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ ነው አለ፡፡
የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ የዝግጅት ስራዎችን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት÷ ፎረሙ “የከተሞች ዕድገት ለከተሞች ልህቀት” በሚል መሪ ሀሳብ ይካሔዳል፡፡
በፎረሙ ከ150 በላይ ከተሞች እና ድርጅቶች እንደሚሳተፉ ገልጸው÷ ለፎረሙ የሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ እንደሆነ አስታውቀዋል።
ፎረሙ የመጭው ዘመን የብልፅግና መዳረሻ የሆኑ ከተሞችን በልምድ ልውውጥ እና በተመጣጣኝ የእድገት ጉዞ እንዲራመዱ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡
በተጨማሪም ወንድማማችነትን በማጎልበት ፉክክርን ማዕከል ያደረገ የስራ ባህልን ለማሳደግ ፎረሙ ጠቃሚ እንደሆነ ተናግረዋል።
ተሳታፊ ከተሞች ምዝገባቸውን እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ማጠናቀቅ እንዳለባቸው ያሳሰቡት ሚኒስትሯ።
ፎረሙ ከህዳር 6 እስከ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።
በሰለሞን ይታየው