Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አንጋፋው ድምጻዊ ማህሙድ አሕመድ ዋንጫ እና የክብር ካባ ሽልማት ተበረከተለት

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፋና ላምሮት 5ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ የፍፃሜ ውድድር ላይ አንጋፋው ድምጻዊ ማህሙድ አሕመድ የዋንጫ እና የክብር ካባ ሽልማት ተበረከተለት።

በደማቅ ሥነ-ሥርዓት በተከናወነው የፍጻሜ ውድድር ላይ አንጋፋው ድምጻዊ ማህሙድ አሕመድ በክብር እንግድነት ተገኝቷል።

ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አንጋፋው ድምጻዊ ማህሙድ አሕመድ የዋንጫ እና የክብር ካባ ሽልማት ተበርክቶለታል።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ አንጋፋው ድምጻዊ ማህሙድ ባስተላለፈው መልዕክት፤ ተወዳዳሪዎች ሰው አክባሪ እንዲሆኑ እና ሥራቸውን እንዲቀጥሉ አሳስቧል።

Exit mobile version