Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ታላቁ የሕዳሴ ግድብ አይቻልም የተባለውን ሰርቶ ማጠናቀቅ እንደሚቻል ማሳያ ነው – አቶ ደስታ ሌዳሞ ‎

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ‎ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ብቻ ሳይሆን አይቻልም የተባለውን ሰርቶ ማጠናቀቅ እንደሚቻል ማሳያ ነው አሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ደስታ ሌዳሞ፡፡

‎የግድቡን መጠናቀቅ አስመልክቶ በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ሕዝባዊ የድጋፍ እና የደስታ መግለጫ ሰልፍ ተካሂዷል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ደስታ ሌዳሞ በድጋፍ ሰልፉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ለግድቡ ግንባታ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደአቅሙ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡

ሁሉም የራሱን አሻራ ያሳረፈበት የግድቡ ግንባታ መጠናቀቁ በጋራ ችለናል የሚለውን የሕብረ ብሔራዊ አንድነታችንና አቋማችንን በጉልህ ያሳየ ነው ብለዋል።

በቀጣይም በጋራ አንችላለን በሚል እሳቤ በሕዳሴ ግድቡ ግንባታ የታየውን መነሳሳትና ቆራጥነት በሌሎች ልማት ዘርፎች ለመድገም በተባበረ ክንድ መነሳት አለብን ነው ያሉት፡፡

‎‎በክልሉ የተለያዩ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ለማስጀመርና የተጀመሩትን ለማጠናቀቅ በጀት መመደቡን ጠቁመዋል፡፡

Exit mobile version