አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስን መከላከል የሚያስችሉ ጥናትና ምርምሮችን እያካሄደ መሆኑን አስታወቀ።
በዩኒቨርሲቲው የምርምርና የማህበረሰበ አቀፍ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር አቢዮት አስረስ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ ያተኮሩ ከ24 በላይ የጥናት ሃሳቦች ቀርበው በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር ከወጣው ትኩረት አቅጣጫ ጋር የሚቀራረቡ 18 ጸድቀው በሂደት ላይ ይገኛሉ ብለዋል።
አሁን ላይም 15 የሚሆኑት ጥናቶች በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ይገኛሉም ነው ያሉት ዶክተር አቢዮት።
ጥናቶቹ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር ባስቀመጠው የትኩረት መስኮች ላይ ያተኮሩ ናቸው ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲው ባለፉት 5 ወራትም ከጥናትና ምርምር ባሻገር ለማህበረሰቡ ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝም አስታውቀዋል።
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አሁን ላይ በሶስቱም ጊቢዎቹ የኮሮና ቫይረስ የለይቶ ማቆያ እና የለይቶ ህክምና አገልግሎት ከመስጠቱም ባሻገር 5 ዞኖች የኮቪድ 19 ምርመራ የሚያገኙበት ማዕከሉን ስራ እስጀምሯል።
በምስክር ስናፍቅ
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

