Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ትኩረት የተደረገባቸው ዘርፎች ለውጥ አምጥተዋል – አምባሳደር ግርማ ብሩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ትኩረት የተደረገባቸው ዘርፎች የተሻለ የምጣኔ ሃብት ዕድገት እንዲመዘገብ ዕድል ፈጥረዋል አሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ አምባሳደር ግርማ ብሩ።

ኢትዮጵያ ተግባራዊ ያደረገችው የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ጨምሮ በግብርና እና በአገልግሎት ዘርፎች ለተሰማሩ ባለሃብቶች ሰፊ ዕድል ይዞ መምጣቱን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ የምጣኔ ሃብት ዕድገት በጥቂት ዘርፎች ላይ የተንጠለጠለ እንደነበር አስታውሰው፥ ከማሻሻያው ትግበራ ወዲህ ለብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ የተለየ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በዚህም ትኩረት የተደረገባቸው ዘርፎች ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅመው ውጤታማ እንዲሆኑና ቀጣይነት ያለው የምጣኔ ሃብት ዕድገት እንዲመዘገብ ዕድል መፍጠሩን አስረድተዋል፡፡

ማሻሻያውን ተከትሎ የውጭ ምንዛሬ ተመን በገበያ ዋጋ እንዲወሰን መደረጉ የወጪ ንግድን ከማበረታታቱም ባሻገር ነጋዴው ትርፋማ እንዲሆን አስችሏል ነው ያሉት።

በተለይም ከውጭ ይገባ የነበረውን ምርት በሀገር ውስጥ በመተካት ረገድ አመርቂ ውጤት ተገኝቷል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Exit mobile version