አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአርሰናል የፊት መስመር ተጫዋች ኖኒ ማዱኬ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ለሁለት ወራት ያህል ከሜዳ እንደሚርቅ ተነግሯል፡፡
ተጫዋቹ ባሳለፍነው እሑድ አርሰናል ከማንቼስተር ሲቲ አንድ አቻ በተለያዩበት የሊጉ የ5ኛ ሳምንት ጨዋታ የጉልበት ጉዳት እንዳጋጠመው ዘ አትሌቲክ ዘግቧል፡፡
የ23 ዓመቱ ተጫዋች ጨዋታውን በቋሚነት ቢጀምርም በ2ኛው አጋማሽ በቡካዮ ሳካ ተቀይሮ መውጣቱ ይታወሳል፡፡