Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

80ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 80ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው።
በጠቅላላ ጉባዔው በፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የተመራ ልዑክ ኢትዮጵያን ወክሎ በመሳተፍ ላይ ይገኛል።
የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶንዮ ጉቴሬዝ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ ጉባዔው እየተካሄደ የሚገኘው ዓለም በአየር ንብረት ለውጥ እና ኢኮኖሚ ቀውስ እንዲሁም ድህነት፣ ረሃብና ጦርነት፣ እየተፈተነች ባለበት ወቅት መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በመንግሥታቱ 80ኛ ዓመት አባል ሀገራት ከመቼውም ጊዜ በላይ አብሮነታቸውን በማጠናከር የተሻለች ዓለም ለመፍጠር በጋራ መሥራት እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋል።
ዓለም እኩልነት እና ፍትሃዊነት ጠፍቶ በተቃራኒው ግለኝነት እና ከባድ ኪሳራን እያስተናገደች መሆኗንም አመልክተዋል፡፡
አሁን ላይ ዓለም ብዝኃነትን በማስተናገድ ረገድ አዎንታዊ ሚና ቢኖረውም በትብብር እና በጋራ እድገት ካልታቀኘ አለመረጋጋት ውስጥ ሊከታት ይችላል ነው ያሉት፡፡
የተቋሙን ሥርዓትና መዋቅር 21ኛውን ክፍለ ዘመን በሚመጥን መልኩ መለወጥ እንደሚገባም አጽንዖት ሰጥተዋል።
ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ምርጫውን ሰላም፣ ፍትህ፣ ዘላቂ ልማት እና ሰብዓዊ ክብር ሊያደርግ እንደሚገባና ለተግባራዊነቱም ቁርጠኝነት እንዲያሳይ ጥሪ አቅርበዋል።
Exit mobile version