Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በደሴ ዙሪያ ወረዳ በትራፊክ አደጋ የ12 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ዙሪያ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ12 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር መሀመድ ሰይድ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት፥ በዛሬው እለት መነሻውን ከመካነ ሰላም ያደረገ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ ደሴ ዙሪያ ወረዳ ልዩ ቦታው ዳባ መግለቢያ አካባቢ አደጋ ደርሶበታል፡፡

በአደጋው የ12 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ሌሎች 49 ሰዎች ከባድና ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል፡፡

ጉዳት የደረሰባቸው ተሳፋሪዎች ህክምና እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን ገልጸው፥ የአደጋው መንሰኤ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

በከድር መሀመድ

Exit mobile version