Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጋቪ በጉዳት ሳቢያ ለአምስት ወራት ከሜዳ ይርቃል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ስፔናዊው የባርሴሎና ኮከብ ጋቪ በጉዳት ምክንያት ለአምስት ወራት ከሜዳ ሊርቅ እንደሚችል ተመላክቷል፡፡
የ21 ዓመቱ አማካይ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር በልምምድ ወቅት በደረሰበት የጉልበት ጉዳት ሳቢያ ነው ከሜዳ የሚርቀው፡፡
ተጫዋቹ በቀኝ እግሩ ጉልበት ላይ የደረሰበትን ጉዳት ተከትሎ ቀዶ ሕክምና የተደረገለት መሆኑን ክለቡ አስታውቋል፡፡
በፈረንጆቹ 2021 የመጀመሪያ ጨዋታውን ለባርሴሎና ዋናው ቡድን ያደረገው ጋቪ በ155 የጨዋታ ተሳትፎ 10 ግቦችን ከመረብ አሳርፏል፡፡
ባርሴሎና በውድድር ዓመቱ አንድ ቀሪ ጨዋታ እያለው በአምስት ነጥብ ከመሪው ሪያል ማድሪድ ዝቅ ብሎ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
በአቤል ነዋይ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Exit mobile version