አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የግብርና ዘርፉን በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ይበልጥ ለማሳደግ በቁርጠኝነት እየተሰራ ነው አለ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ፡፡
የክልሉ ግብርና ዘርፍ የ10 ዓመት የግብርና ትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታ የጥናት ውጤት ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር በዚህ ወቅት እንዳሉት÷በክልሉ በግብርና ዘርፍ የመልማት አቅም ያላቸውን እምቅ ሃብቶች በመለየት እየተሰራ ነው፡፡
ዘርፉን በማዘመን ምርታማነትን ለማሳደግ የተለያዩ ኢኒሼቲቮች በመቅረጽ በተሰራው ሥራ ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበ ነው ብለዋል፡፡
ለአብነትም የአዳዲስ ምርቶች መጀመር፣ የምርት ምጣኔ ማደግና የአምራቾች ተጠቃሚነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ጠቅሰዋል፡፡
እነዚህን ውጤቶች ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በማጥናትና በመተግበር የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥም ላለፉት 6 ወራት የተካሄደው የጥናት ውጤት መገምገሙን አንስተዋል፡፡
ጥናቱ በክልሉ የቤተሰብና የማሕበረሰብ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ከማገዝ ባሻገር ሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገትን ማሳለጥ ያስችላል ነው ያሉት፡፡
የክልሉ ግብርና ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች የ10 ዓመት ክልላዊ የእድገት ፍኖተ ካርታን በውል ተረድተው መተግበር እንዳለባቸው ማስገንዘባቸውንም የክልሉ ግብርና ቢሮ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!