Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዳዲስ ሹመት ሰጠ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥቷል።
በዚህም መሰረት አቶ ሐፍታይ ገብረእግዚያብሔር የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ የቄራዎች ድርጅት ስራ አስኪያጅ፣ አቶ ዋለልኝ ደሳለኝ የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት አስተዳደር ባለስልጣን ምክትል ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል።
እንዲሁም ወይዘሮ ነስትሆ አብዲ የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት አስተዳደር ባለስልጣን ፅ/ቤት ኃላፊ በመሆን መሾማቸውን የከንቲባ ጽህፈት ቤት ለፋና ዲጂታል ገልጿል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Exit mobile version