አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ የተገነባው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በዛሬው ዕለት ተመርቋል፡፡
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ መርቀው ሥራ አስጀምረዋል፡፡
ማዕከሉ አራት የፌደራል እና ስድስት የክልል ተቋማት አገልግሎቶችን በአንድ ጣሪያ ሥር መያዙ ነው የተገለጸው፡፡
በዚህም ከ15 በላይ አገልግሎቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በታገዘና በተቀላጠፈ ዘመናዊ አሰራር በአንድ ማዕከል መስጠት እንደሚያስችል ተመላክቷል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!