አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በሆሳዕና ከተማ የተገነባውን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በዛሬው ዕለት መርቀው ስራ አስጀምረዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ማዕከሉ አምስት የፌደራልና ሁለት የክልል ተቋማትን የያዘ ሲሆን፥ 20 አገልግሎቶችን መስጠት ያስችላል፡፡
ተቋሙ ወደፊት ከ60 በላይ አገልግሎት መስጠት የሚችል መሆኑን ገልጸው፥ በክልሉ የአንድ ማዕከል አገልግሎቱን ለማስፋፋት በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት፡፡
የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ መጀመር አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን ፍትሃዊ፣ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋዮችን እርካታ ከፍ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡
በሆሳዕና ከተማ ከተገነባው ማዕከል ልምድ በመውሰድ በዚህ ዓመት መጨረሻ በክልሉ ሰባት የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫዎች እንደሚኖሩ ጠቁመዋል።
የተጀመሩ ስራዎችን በማጠናከር የህዝብ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ተግባራት ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!