Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የምዘና ሥርዓትን በማጠናከር ውጤታማ ሥራዎችን መከወን ይገባል – አቶ አረጋ ከበደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል የ2017 በጀት ዓመት የክልል ተቋማት መሪዎች የምዘና ውጤት ግምገማ እና የዕውቅና መርሐ ግብር ተካሂዷል።
የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በዚህ ወቅት ÷ የምዘና ሥርዓትን እያጠናከሩ ውጤታማ ሥራዎችን መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
ምዘናዎችንና የሚገኙ ውጤቶችን ከክልሉ ሥራዎች ጋር ማገናዘብ እንደሚገባ ጠቁመው ÷ ይህም የተሻለ ሥራ ለመሥራትና ክልሉን ውጤታማ ለማድረግ ያግዛል ብለዋል፡፡
እያንዳንዱ ተቋም የተሻለ ሲፈጽም የተሻለ ክልል መገንባት ይቻላል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ÷ የምዘና ሒደቱን ዘመናዊ ማድረግ እንደሚገባ አመላክተዋል።
በሚቀጥሉት ጊዜያት ክፍተቶችን ማስተካከል እና ጥንካሬዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ ፍስሃ ደሳለኝ በበኩላቸው÷ መመሪያውን መሠረት በማድረግ ተቋማት መመዘናቸውን አስረድተዋል።
ትልቅ ሕዝብ የምናሥተዳድር መሪዎች ስለሆንን ሥራዎቻችንም ትልቅ መሆን አለባቸው ፤ ምዘና ማድረግ ተቋምና መሪ ለመገንባት ያስችላል ብለዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ በዓመቱ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ተቋማት ዕውቅና እና ሽልማት እንደተበረከተላቸው አሚኮ ዘግቧል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
Exit mobile version