Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በድሬዳዋ የደመራ በዓል የሚከበርበትን ስፍራ የማፅዳት መርሐ ግብር ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር ከኃይማኖት አባቶች ጋር በመሆን በከተማዋ የደመራ በዓል የሚከበርበትን ስፍራ የማጽዳት መርሐ ግብር አከናውነዋል፡፡

በዚሁ ወቅት ድሬዳዋ ሁሉም እምነቶች በፍቅር፣ በአብሮነትና በሰላም የሚኖሩባት ከተማ መሆኗ የተገለጸ ሲሆን፥ እንደነዚህ አይነት በዓላት ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን እንደሚያጠናክሩ ተጠቁሟል።

በፅዳት ዘመቻው የተሳተፉ የተለያዩ እምነት ተከታዮች በድሬዳዋ ሁሉም በዓል በአብሮነት እንደሚከበር ጠቅሰው፥ በዓሉ የፍቅር፣ የሰላምና የአብሮነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የፀጥታ አካላት እና በጎ ፍቃደኛ ወጣቶችም ተሳትፈዋል።

Exit mobile version