Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በጋምቤላ ከተማ የመስቀል ደመራ በዓልን በማስመልከት የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የመስቀል ደመራ በዓልን በማስመልከት የጋምቤላ ክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የጽዳት ዘመቻ በጋምቤላ ከተማ ተካሂዷል።

‌‎የጽዳት ዘመቻው የመስቀል ደመራ በዓል የሚከበርበት ቦታን ጨምሮ በከተማዋ ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ ነው የተካሄደው።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኡቶው ኡኮት እንዳሉት፤ ነዋሪውን በማሳተፍ የመስቀል ደመራ በዓልን በማስመልከት የጽዳት ዘመቻው ተካሂዷል።

‌‎የጽዳት ዘመቻውን ማካሄድ ህዝቡ የትብብርና የአብሮነት እሴቶቹን ይበልጥ ለማጠናከር ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version