አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመስቀል እና ኢሬቻ በዓላትን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋርተዋል፡፡
ከንቲባዋ ባስተላለፉት መልዕክት÷ ዛሬ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች ዘወትር በዓል በመጣ ቁጥር እንደምናደርገው የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላትን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋርተናል ብለዋል።
በዚህ ተግባር የቆየውን የመደጋገፍ እና ተካፍሎ የመኖር ባህል ከሰዉ ተኮር እሳቤዎቻችን ጋር አቆራኝተን የተቸገሩትን የመርዳት እሴቶቻችንን እያዳበርንበት ነዉ በማለት ገልጸው፤ ይህንን በጎ ተግባር እየደገፉ የሚገኙ አካላትን አመስግነዋል።