Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሚኒስቴሩ ከተጠሪ ተቋማት፣ ከክልል እና ከተማ አስተዳደር የጸጥታና ደህንነት ተቋማት ጋር ያካሄደውን ውይይት አጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የሰላም ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት፣ ከክልል እና ከተማ አስተዳደር የጸጥታና ደህንነት ተቋማት ጋር ለስድስት ቀን ሲያካሂድ የነበረውን ውይይት በስኬት ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡

ውይይቱ የህግ ማስከበርና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች የተዳሰሱበት ሲሆን በፌደራል፣ በክልልና በከተማ አስተዳደሮች ባለፈው በጀት ዓመት በጸጥታና ደህንነት ዘርፍ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን አፈጻጸም ጠንካራና ደካማ ጎኖች በጥልቅ ገምግሟል፡፡

በቀጣዩ የበጀት ዓመት ዝርዝር እቅድ ፣ በቀጣይ 10 አመት መሪ እቅድ ላይ እና ህብረተሰብን ያማከለ የሰላም ግንባታ ዙሪያም ተወያይቷል፡፡

እንዲሁም የሰላም ቤተሰቦች ኃላፊነታቸውን በሚወጡበት ወቅት ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ ውጥረቶችን ለመቀነስ የሚያግዝ የስትረስ ማኔጅመንት ስልጠና መውሰዳቸውም ታውቋል፡፡

የስድስት ቀኑ መርሃ ግብርም የሸገርና እንጦጦ ፓርክ ፕሮጀክቶችን በመጎብኘት እንዲሁም የችግኝ ተከላ በማካሄድ መጠናቀቁን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version