Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያዊቷ ፅጌ ካሕሳይ በዓለም የብስክሌት ሻምፒዮና ከአፍሪካ በቀዳሚነት አጠናቀቀች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያዊቷ ፅጌ ካሕሳይ በዓለም የብስክሌት ሻምፒዮና በወጣቶች ዘርፍ ከአፍሪካ አንደኛ በመሆን አጠናቀቀች።

የዓለም የብስክሌት ሻምፒዮና በሩዋንዳ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል።

በዚህም ኢትዮጵያዊቷ ብስክሌተኛ ፅጌ ካሕሳይ 74 ኪሎ ሜትር በሸፈነው የወጣቶች የጎዳና ውድድር ከአፍሪካ አንደኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች።

ከፍተኛ ፉክክር በታየበት በዚህ ውድድር ላይ ከዓለም 7ኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀች ሲሆን፥ ከዚህ ቀደም በወጣቶች የግል ሰዓት ውድድር ከአፍሪካ በቀዳሚነት ማጠናቀቋ ይታወሳል።

Exit mobile version