Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የማዕከላዊ ዕዝ ጊቤ ኮር የምሥረታ በዓል እየተከበረ ነው 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀገር መከላከያ ሠራዊት የማዕከላዊ ዕዝ ጊቤ ኮር አራተኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በጊምቢ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።

የኮሩ የምስረታ በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበር ሲሆን የበዓሉ አካል የሆነ የፓናል ውይይት የማዕከላዊ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ እና ሌሎች ከፍተኛ መኮንኖች በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ እንደተገለጸው፤ ጊቤ ኮር በፈተና ውስጥ የተወለደ ነው።

ኮሩ ለሀገር ሰላም እና አንድነት መጠናከር ትልቅ ዋጋ የከፈለ መሆኑ ተገልጿል።

አሁንም ተልዕኮውን በብቃት በመወጣት የድርሻውን በመወጣት አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ተመላክቷል።

የጊቤ ኮር አራተኛ ዓመት የምስረታ በዓል ከዛሬ ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች በጊምቢ ከተማ እና በጊምቢ ስታዲየም እንደሚከበር ታውቋል።

በገላና ተስፋ

Exit mobile version