Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አስቶንቪላ ፉልሃምን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አስቶንቪላ ፉልሃምን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

በቪላ ፓርክ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ፉልሀም በራውል ሄሚኔዝ ግብ ቀዳሚ ቢሆንም ባለሜዳው አስቶንቪላ ዋትኪንስ፣ ማክጊን እና ቡዌንዲያ ባስቆጠሯቸው ግቦች ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።

የሊጉ መርሃ ግብር ሲቀጥል ምሽት 12 ሰዓት ከ30 ኒውካስትል ዩናይትድ ከአርስናል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

Exit mobile version