Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ቻይና እና ሰሜን ኮሪያ ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ቻይና እና ሰሜን ኮሪያ ያላቸውን ሁለንተናዊ ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ቁርጠኞች ነን አሉ፡፡

የቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ከሰሜን ኮሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቾይ ሰን ሁይ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ሊ ኪያንግ በዚህ ወቅት÷ ቻይና እና ሰሜን ኮሪያ ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዳላቸው አስታውሰዋል፡፡

ቤጂንግ በሁሉም ዘርፍ ከፒዮንግያንግ ጋር ያላትን ግንኙነትና ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል፡፡

ቾይ ሰን ሁይ በበኩላቸው÷ ሰሜን ኮሪያ ከቻይና ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር የማይናወጥ አቋሟ ነው ብለዋል፡፡

በሀገራቱ መካከል ያለውን የሕዝብ ለሕዝብ እና የባህል ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ መስራት እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በሀገራቱ መሪዎች የተፈጸሙ ስምምነቶችን ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰሩ መግለጻቸውንም ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

Exit mobile version