Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያ ዋንጫ የሚጀምርበት ቀን ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የ2018 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ዋንጫ የሚጀመርበትን ቀን ይፋ አድርጓል።

ፌደሬሽኑ እንደገለጸው ÷ የዘንደሮው የኢትዮጵያ ዋንጫ ጨዋታ በመጪው ጥቅምት 9 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ይጀመራል፡፡

በዚህ መሰረትም የኢትዮጵያ ዋንጫ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ከጥቅምት 9 እስከ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡

በ1ኛ ዙር የኢትዮጵያ ዋንጫ ጨዋታ የከፍተኛ ሊግ ተሳታፊ ቡድኖች የዙር ውድድር በሚያካሂዱበት ከተማ በየምድባቸው የእርስ በርስ ጨዋታ በማድረግ አሸናፊ ቡድኖች ወደ 2ኛው ዙር ያልፋሉ፡፡

በዚህም ወደ ሁለተኛ ዙር የሚቀላቀሉት የከፍተኛ ሊግ ተሳታፊ ቡድኖች በቀጥታ ከፕሪሚየር ሊግ ቡድኖች ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

በ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ የሚሆነው ቡድንም ኢትዮጵያን በመወከል በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የሚሳተፍ ይሆናል፡፡

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version