አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የጎብኚዎችን ቀልብ የሚስቡ ታሪካዊ፣ ባህላዊና ተፈጥሯዊ መዳረሻዎች ያላት ሀገር ነች።
አነዚህን እምቅ የተፈጥሮና ታሪካዊ ቅርሶች ለመጎብኘት በየዓመቱ ከአንድ ሚሊየን የላቁ የውጭ ሀገር ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ።
ጎብኚዎቹ በአብዛኛው በዩኔስኮ የተመዘገቡ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ እንዲሁም በምዝገባ ሂደት ላይ ያሉ ሰው ሰራሽና ባህላዊ ቅርሶችን መጎብኘት ደግሞ ምርጫቸው ነው፡፡
ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ለሁለተኛ ጊዜ የመጡት አሜሪካዊው ቱሪስት ማርኪያ ዳርም በመጀመሪያ ጉብኝታቸው የላሊበላ ወቅር አብያተ ክርስቲያናትን፣ የጥምቀት በዓል አከባበርንና የኦሞ ሸለቆ መመልከታቸውን አስታውሰዋል፡፡
ኢትዮጵያን ከረገጡበት ቀን አንስቶ የተመለከቱት የማህበረሰቦች ባህልና እሴት እንዲሁም የማይረሳ መስተንግዶ በድጋሚ እንዲመጡ እንዳነሳሳቸው እና በቀደመ ቆይታቸው ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ ባህል፣ ታሪክ፣ ቅርስና የተፈጥሮ መስህብ መመልከታቸውን ጠቅሰዋል፡፡
አውስትራሊያዊው ኒክ ድን በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያ በነበራቸው የቆይታ ጊዜ የኦሞ ሸለቆና ሌሎች መዳረሻዎችን መመልከታቸውን ገልጸዋል፡፡
በጎበኟቸው አካባቢዎች አስደናቂ የማሕበረሰብ አኗኗር፣ ባህልና እሴት በመመልከት የማይረሳ ልምድ መቅሰማቸውን ተናግረዋል፡፡
ስፔናዊው ፓብሎ ዊድን እንደገለጹት÷ በኢትዮጵያ ዓይን የሚማረኩ፣ የውስጥ እርካታ የሚሰጡና መንፈስን የሚያድሱ ባህላዊና ታሪካዊ የተፈጥሮ መስህቦችን ጎብኝተዋል፡፡
ጎብኝዎቹ ኢትዮጵያ እምቅ የሆነ ታሪካዊ፣ ባህላዊና ተፈጥሯዊ የቱሪስት መዳረሻ የታደለች ሀገር መሆኗን ማመላከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በአዲስ አበባ የተለያዩ የቱሪስት መዳረሻዎች መኖራቸውን የጠቀሱት የውጭ ሀገር ጎበኚዎች÷ በተለይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚዬም በአፍሪካ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፅዕኖ ያላቸው ቅርሶች፣ ቅሪተ አካላትና የጥናት ግኝቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል።
ነዋሪነታቸው በአሜሪካ ያደረጉት ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ወይዘሮ ወርቅነሽ ዘውዴ ዘወትር ወደ ሀገራቸው ሲመጡ አዲስ ስሜት እንደሚፈጠርባቸው ተናግረው÷ የተለያዩ ቅርሶች፣ ታሪኮች ባህሎችና የተለየ የአየር ጸባይ የተላበሰች ውብ ሀገር መሆኗንም አንስተዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!