አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የ2ኛ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች ይደረጋሉ፡፡
ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ላይ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ቤኔፊካን እየመሩ በስታምፎርድ ብሪጅ የቀድሞ ክለባቸው ቼልሲን የሚገጥሙበት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ፖርቹጋላዊ አሰልጣኝ ከምሽቱ ጨዋታ አስቀድሞ ስለ ቀድሞ ክለባቸው በሰጡት አስተያየት፥ ቼልሲ ትልቅ ክለብ እንዲሆን የላቀ ሚና እንደነበራቸው አስታውሰዋል፡፡
እኔ ሁሌም ሰማያዊ ነኝ፥ ነገር ግን በዛሬ ምሽቱ ጨዋታ ትኩረቴ ቤኔፊካን አሸናፊ ማድረግ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ጨዋታ አስቀድሞ ምሽት 1 ሰዓት ከ45 የመድረኩ ኃያል ክለብ ሪያል ማድሪድ 13 ሰዓታት የሚፈጅ ረጅም በረራ በማድረግ የካዛኪስታኑን ካይራት አልማቲ ይገጥማል፡፡
በተመሳሳይ ምሽት 1፡45 የጣሊያኑ አታላንታ የቤልጂየሙን ክለብ ብሩጅ በሜዳው ያስተናግዳል፡፡
ምሽት 4 ሰዓት ላይ ሊቨርፑል ወደ ቱርክ አቅንቶ ጋላታሳራይን የሚገጥም ሲሆን፥ ቶተንሃም ወደ ኖርዌይ ተጉዞ ከቦዶ ግሊምት ጋር ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
የአምናው የፍጻሜ ተፋላሚ ኢንተር ሚላን ከቼክ ሪፐብሊኩ ስላቪያ ፕራግ፣ ባየርን ሙኒክ ከቆጵሮሱ ፓፎስ፣ አትሌቲኮ ማድሪድ ከኢንትራክት ፍራንክፈርት፣ ማርሴ ከአያክስ አምስተርዳም ሌሎች የዛሬ ምሽት ጨዋታዎች ናቸው፡፡
በኃይለማሪያም ተገኝ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!