Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሸካቾ ዘመን መለወጫ “ማሽቃሬ ባሮ” በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሸካቾ የዘመን መለወጫ “ማሽቃሬ ባሮ” በዓል በጌጫ ከተማ በተለያዩ ሥነ ሥርዓቶች እየተከበረ ነው።

አንድነት፣ መተሳሰብና መረዳዳት የሚንጸባረቅበት የ”ማሽቃሬ ባሮ” በዓል ላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)ን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

“ማሽቃሬ ባሮ” በአዲስ መንፈስ በፍቅርና በአንድነትን ከጠንካራ የሥራ ባህል ጋር ቀጣዩን ዓመት ለማሳለፍ “ትሞና ሼሮ” የተሰኘ የሥራና የሥነ ምግባር መመሪያ የሚተላለፍበት ቱባ ዕሴቶችን የያዘ በዓል መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በእምቅ የተፈጥሮ ሀብትና አረንጓዴነት የሚታወቀው ሸካ ዞን፣ ማርና ቅመማ ቅመም በስፋት የሚመረትበት፣ የተፈጥሮ መስህብ ስፍራዎችን በብዛት አቅፎ የያዘ ነው።

Exit mobile version