Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሆረ ፊንፊኔ የሚከበርበትን ኢሬቻ ፓርክ የማፅዳት ስራ  እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል የሚከበርበትን ኢሬቻ ፓርክ የማፅዳት ስራ  እየተከናወነ ይገኛል።

ከአዲስ አበባ ሁሉም ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ አመራሮች፣ አርቲስቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በፅዳት ስራው ተሳታፊ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፅዳት አስተዳደር  ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ገዛኸኝ ደሲሳ እንዳሉት÷ የኢሬቻ ፓርክን የማስዋብና ፅዳቱን የመጠበቅ ስራ በዓሉ ከመድረሱ በፊት ሲሰራ ቆይቷል።

ዘንድሮ ሆረ ፊንፊኔ ቅዳሜ መስከረም 24፤ እንዲሁም ሆረ ሀርሰዴ በማግስቱ መስከረም 25 ቀን 2018 ዓ.ም ‘ኢሬቻ ለሀገር ማንሠራራት’ በሚል መሪ ሀሳብ  ይከበራል።

ከዚህም ባሻገር እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ አካባቢዎች እሴቱን ጠብቆ የሚከበር ይሆናል፡፡

ሰላም፣ እርቅ፣ ፍቅር፣ ወንድማማችነት እና አንድነት የኢሬቻ በዓል ዋና መገለጫዎች ናቸው።

በእዮናዳብ አንዱዓለም

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version