Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢሬቻ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር ሁሉም ተሳታፊ ሚናውን እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ተሳታፊ ሚናውን መወጣት አለበት አለ።
የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት የ2018 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል አከባበርን በተመለከተ በቢሾፍቱ ከተማ መግለጫ ሰጥቷል።
በመግለጫውም፤ ‘ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት’ በሚል መሪ ሀሳብ የሚከበረው የዘንድሮ የኢሬቻ በዓል ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በተመረቀ ማግስት መሆኑ ለየት ያደርገዋል።
በዓሉ እንደተለመደው በድምቀት እንዲከበር ዝግጅት መደረጉን የገለጸው ህብረቱ፤ በዓሉ ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር ታዳሚዎች የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።
በዓሉ ሲከበር የሀገርን አንድነት ይበልጥ በሚያጎሉ እና ለሀገር ማንሰራራት በሚያግዝ መልኩ መሆን እንዳለበትም አስገንዝቧል።
ኢሬቻ የሰላም፣ የእርቅና የአብሮነት በዓል ነው ያለው ህብረቱ፤ የሀገሪቱ ብሔር ብሔረሰቦች በስፋት የሚሳተፉበት ነው ብሏል።
የዘንድሮ ኢሬቻ በዓል ሆረ ፊንፊኔ ቅዳሜ መስከረም 24፤ እንዲሁም ሆረ ሀርሰዴ በማግስቱ መስከረም 25 ቀን 2018 ዓ.ም ይከበራል።
በታምራት ደለሊ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
Exit mobile version