አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሐረሪ ክልል በወጣቶች ስብዕና ልማት ማዕከላት ወጣቶችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል አለ የሐረሪ ክልል ወጣቶች ስብዕና ልማት ማዕከል፡፡
የማዕከሉ ሥራ አስኪያጅ ኢምራን አብዱሰመድ እንዳሉት ÷ የክልሉ መንግስት ወጣቶችን በስብዕና ማዕከላት ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው።
በማዕከላቱ በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ለወጣቶች 16 አይነት አገልግሎቶች እንዲሰጡ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
ማዕከላቱ ወጣቶች ጊዜያቸውን በአግባቡ በመጠቀም ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩና ጊዜያቸውን በአልባሌ ቦታ እንዳያባክኑ ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክተዋልም ነው ያሉት፡፡
በማዕከላቱ ወጣቶችን በሥነ ምግባር ከማነፅ ባሻገር ዕውቀት የሚገበዩበትን ሥርዓት ለመፍጠር በትብብር እንደሚሰራ አመልክተዋል፡፡
የወጣቱን ማሕበራዊ፣ ፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥም የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ማለታቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!