Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አርቲስት ፍሬህይወት ባህሩ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

‎አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አርቲስትና ኮሜዲያን ፍሬሕይወት ባህሩ ባጋጠማት ድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡

‎አርቲስቷ የቀለጠው መንደር፣ ፎርፌ፣ ረመጥ፣ ነቃሽ እና ሌሎች በርካታ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በተሰሩ ቴአትሮች ላይ ተውናለች ።

‎‎አርቲስት ፍሬህይወት በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በውዝዋዜ እና ዳንስ ተቀጥረው ችሎታቸውን በመድረክ ካሳዩት ከያኒያን መካከል አንዷ ነበረች።

‎በሀገር ፍቅር ቴአትር ለበርካታ ዓመታት በሙያዋ ያገለገለችው አርቲስቷ፤ በበርካታ ፊልሞች፣ የቴሌቪዥን ድራማ እና የሙዚቃ ክሊፖች ላይ በትወና መሳተፏን የሀገር ፍቅር ቴአትር መረጃ አመልክቷል።

Exit mobile version