አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዳንጎቴ ግሩፕ አፍሪካን አፍሪካዊያን ናቸው የሚያለሙት ብሎ ያምናል አሉ የግሩፑ ባለቤት አሊኮ ዳንጎቴ።
በሶማሌ ክልል የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ከዳንጎቴ ግሩፕ ጋር በመተባበር የሚገነባው የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ መሰረተ ድንጋይ በዛሬው ዕለት ተቀምጧል።
የዳንጎቴ ግሩፕ ባለቤት አሊኮ ዳንጎቴ በዚህ ወቅት÷ አሁን ላይ ኢትዮጵያ ኢንቨስተሮችን መሳብ የምትችል ሀገር ሆናለች፤ ለዚህም የሀገሪቱ መንግሥት ያደረገው ጥረት የሚደነቅ ነው ብለዋል።
የዚህ ታሪካዊ ፕሮጀክት አካል በመሆኔ ኩራት ተሰምቶኛል፤ ፕሮጀክቱን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ የሚጠበቅብንን ሁሉ እናደርጋለን ነው ያሉት።
በቅርቡ የተጠናቀቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በመመረቁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉት ባለሃብቱ÷ ግድቡን በራስ አቅም መገንባት መቻሉ እኛ አፍሪካውያን በራሳችን ምንም ነገር ማድረግ እንደማያቅተን ማሳያ ነው ሲሉም አውስተዋል።
የዳንጎቴ ግሩፕም ኢትዮጵያ በምግብ ራስን ለመቻል በምታደርገው ጉዞና የኢነርጂ ትራንስፎርሜሽን ያካበተውን የረጅም ጊዜ ልምድ አሟጦ በመጠቀም የሀገሪቱን እድገት ለማፋጠን እንደሚሰራ አመላክተዋል።
የዳንጎቴ ግሩፕ አፍሪካን አፍሪካዊያን ናቸው የሚያለሙት ብሎ እንደሚያምን አጽንኦት ሰጥተዋል።
የዳንጎቴ ግሩፕ በርካታ ትላልቅ ፕሮጀክቶች መገንባቱን አስታውሰው÷ ኢንቨስተሮች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ኢንቨስት እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።
በሶስና አለማየሁ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!