Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ የወሰደቻቸውን ማሻሻያዎች ውጤት አምጥተዋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ የወሰደቻቸውን ሀገር በቀል ማሻሻያዎች ውጤት አምጥተዋል አሉ በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር)።

የፓኪስታን መንግሥት ኢትዮጵያ በሀገር በቀል የልማት ሞዴሎች የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ያስመዘገበችው ስኬት የሚደነቅ እና ለሌሎች በተሞክሮነት የሚጠቀስ መሆኑም ተገልጿል።

አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር) ከፓኪስታን የብሔራዊ ምግብ ዋስትና እና ምርምር ፌዴራል ሚኒስትር ራና ታንቪር ሁሴን ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በግብርና እና በእንስሳት ሀብት ዘርፎች የሁለትዮሽ ትብብር ስለሚጠናከርበት ሁኔታ መክረዋል።

ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ የወሰደቻቸውን ሀገር በቀል ማሻሻያዎች ውጤት ማምጣታቸው የገለጹት፤ አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር) አረንጓዴ ዐሻራ እና የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብሮች ስኬታማ ናቸው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከጠቅላላ የኃይል አቅርቦቷ 98 በመቶ የሚሆነውን በንጹሕና ታዳሽ ኃይል በመሸፈን ኢኮኖሚዋን እያሰደገች መሆኗን ጠቁመው፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ እና የኦጋዴን የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት መጀመር በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ እና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፎች ምርታማነትን እንደሚያሳድግም ገልጸዋል።

ራና ታንቪር ሁሴን በበኩላቸው ሁለቱ ሀገራት የምግብ ዋስትና ተግዳሮትን በጋራ ለመፍታት ሰፊ ዕድል እንዳላቸው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ የቡና ወጪ ንግድ ስኬት የጠንካራ ፖሊሲ ውጤት መሆኑን ጠቁመዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version