አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በድምቀት እንዲከበር የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ ባስተላለፉት መልዕክት፥ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በዓል እንግዶችን በመቀበልና በማስተናገድ ላሳዩት ትብብርና ፍቅር አመስግነዋል፡፡
የኦሮሞን ህዝብ ደስታ ለመጋራት በበዓሉ ላይ ለታደሙ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች ተወካዮች ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ ነው ያሉት፡፡
በተመሳሳይ በዓሉ በድምቀት እንዲከበር ላደረጉ የጸጥታ አካላት እንዲሁም ባህሉን ለዓለም ለማሳየት እገዛ ላደረጉ የሀገር ውስጥና የውጭ መገናኛ ብዙሃን ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የኢሬቻ በዓልን በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) እንዲመዘገብ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡