Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ቼልሲ ከሊቨርፑል – የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ7ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቼልሲ ከሊጉ መሪ ሊቨርፑል የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡

በፕሪሚየር ሊጉ ካስተናገደው ሁለት ተከታታይ ሽንፈት መልስ ሊቨርፑልን በስታምፎርድ ብሪጅ የሚያስተናግድበት ጨዋታ ምሽት 1፡30 ይጀምራል፡፡

ከዚህ ጨዋታ አስቀድሞ ቀን 11 ሰዓት ላይ አርሰናል በውጤት እጦት ውስጥ የሚገኘውን ዌስትሃም ዩናይትድን ያስተናግዳል፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት ማንቼስተር ዩናይትድ ሰንደርላንድን በኦልድትራፎርድ የሚያስተናግድ ሲሆን፥ ጨዋታው የመሰናበት ስጋት ላለባቸው ሩበን አሞሪም ወሳኝ መሆኑ ተዘግቧል፡፡

ቶተንሃም ሆትስፐር ከሜዳው ውጭ ሊድስ ዩናይትድን የሚገጥምበት የዕለቱ የመጀመሪያ መርሐ ግብር ቀን 8 ሰዓት ከ30 ላይ ይደረጋል፡፡

Exit mobile version