አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ7ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ አምስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
በዚህ መሰረትም ቀን 10 ሰዓት ላይ አስቶንቪላ ከበርንሌይ፣ ኤቨርተን ከክሪስታል ፓላስ፣ ኒውካስል ዩናይትድ ከኖቲንግሃም ፎረስት እንዲሁም ዎልቭስ ከብራይተን ይጫወታሉ፡፡
በተጨማሪም ምሽት 12፡30 ማንቼስተር ሲቲ ወደ ለንደን አቅንቶ ብሬንትፎርድን በቴክ ኮሚኒቲ ስቴዲየም የሚገጥም ይሆናል፡፡
ባለፉት ጨዋዎች 10 ነጥብ በመሰብሰብ በሊጉ 8ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት ሲቲዝኖቹ ÷ የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፉ ደረጃቸውን ወደ 5 ከፍ ማድረግ ይችላሉ፡፡