Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በክልሉ ቴክኖሎጂ መር የወንጀል ምርመራ ሒደት እንዲጠናከር እየተሰራ ነው – ኮሚሽር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ቴክኖሎጂ መር ዘመናዊ የወንጀል ምርመራ ሒደት እንዲጠናከር እየተሰራ ነው አሉ የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር)፡፡
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የጀመረው የሪፎርም ሥራ ዲጂታላይዜሽን ማብሰሪያና የአዲስ ሕንጻ ምረቃ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
በመርሐ ግብሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና ሌሎች ከፍተኛ የፌደራልና የክልሉ መንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
ኮሚሽር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ የክልሉን ፖሊስ ክልሉ አሁን ያለበትን የሰላምና የልማት ጥያቄዎች ሊመልስ በሚችል መልኩ ለማደራጀት እየተሰራ ነው፡፡
በተከናወነው ተቋማዊ ሪፎርም ፖሊስ የአሠራር ነጻነት እንዲኖረውና ተጠሪነቱ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መሆኑ ለለውጥ ሥራዎች መሠረት ጥሏል ብለዋል፡፡
ይህን ተከትሎም የክልሉ ፖሊስ የተደራጁ ወንጀሎችን እና የጸረ ሰላም ኃይሎችን እንቅስቃሴ በቀላሉ ለመከላከል የሚያስችል አቅም እየፈጠረ ይገኛል ነው ያሉት፡፡
ተቋሙ ዘመናዊ አሰራርን እንዲተገብር የዲጂታል እና ተመሳሳይ ዘመናዊ አሰራሮችን እንዲከተል እየተሰራ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡
ዛሬ የተመረቀው ሕንጻም በወንጀል መከላከል እና ምርመራ እንዲሁም ለአጠቃላይ ዘመናዊና ተቋማዊ ልህቀት የእተሰራ መሆኑን እንደሚያመላክት ጠቅሰዋል፡፡
ፖሊስ ሕዝባዊ ቅቡልነት እንዲኖረው እየተደረገ ያለው ጥረት ለውጥ እያሳየ ነው ያሉት ኮሚሽር ዘላለም (ዶ/ር) ÷በሪፎርም ሥራዎች ዘመናዊ የወንጀል ምርመራ ሒደት እንዲጠናከር እየተሠራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

በለይኩን ዓለም

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Exit mobile version