አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የባሕር ዳር ስማርት ከተማ ጉዞዋንና የልማት ስራዎችን እናፋጥናለን አሉ የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው።
አቶ ጎሹ እንዳላማው የባሕር ዳር ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተመርቆ ስራ በጀመረበት ወቅት እንዳሉት÷ በከተማዋ እየተከናወነ በሚገኘው ዘርፈ ብዙ የልማት ሥራዎች ነዋሪዎች ደስተኛ ናቸው።
በሕዝባዊ ውይይቶች በመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ተደጋጋሚ ቅሬታ ሲቀርብ እንደነበር አስታውሰው÷ ችግሮችን ለመቅረፍ በከተማዋ በርካታ ስራ መሰራቱን ጠቅሰዋል።
የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በጥናት በመለየት መፍትሔ መወሰድ መጀመሩን ተናግረዋል።
የመንግሥት አገልግሎትን ይበልጥ ለማሳለጥ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት 12 የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት አገልግሎታቸውን ይዘው እንዲገቡ መመረጣቸውንና 92 አገልገሎቶች መለየታቸውን አመላክተዋል።
ለዘጠኝ ተቋማት 48 አገልግሎቶችን ለማስጀመር ዝግጅት መደረጉን አንስተው÷ የከተማዋ ነዋሪ ከሰኞ ጀምሮ በመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ማግኘት እንደሚችል ጠቁመዋል።
በለይኩን ዓለም
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!