Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ም/ቤቶች የ2018 የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ በዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-

👉 የኢትዮጵያ የጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና በመደርጀት ላይ ይገኛል ፤ ይህ ስትራቴጂያዊ ምርጫም ኢትዮጵያን ከታዛቢነት ወደ አጀንዳ ተላሚነትና ተጽዕኖ ፈጣሪነት ለማሸጋገር አስችሏል፣

👉 በድንበር ተሻጋሪ ሀብቶቿ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ስትቀበል፤ ከዚሁ ጎን ለጎን አስተማማኝ የባሕር በር የማግኘት መብቷን ማረጋገጥ ይጠበቅባታል፣

👉 የኢትዮጵያ የሕልውና መሰረት በሆኑት በሁለቱ ትላልቅ የውሃ ሃብቶች ዙሪያ መንግስት ያልተቋረጠ ሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፣

👉 እስካሁን በተደረጉ ጥረቶችም ሦስት ጉልህ ውጤቶች ተመዝግበዋል፣

1️⃣ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያጋጠሙትን ፈተናዎች በጥበብ በማለፍ ማጠናቀቅና ለምረቃ ማብቃት ተችሏል፣

2️⃣ አስተማማኝና ዘላቂነት ያለው የባህር በር የማግኘት ጉዳይ ከፍ ወዳለ ደረጃ ተሸጋግሯል፤ በጉዳዩ ዙሪያ በዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ዘንድ ቅቡልነቱ እያደገ መጥቷል፣

3️⃣ በውጭ ሀገራት ለእንግልትና ለችግር የተጋለጡ ዜጎቻችን በክብር ወደ ሐገር እንዲመለሱ ተደርጓል፤ በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል፣

በኃይለማርያም ተገኝ

Exit mobile version