አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡
ምክር ቤቱ ለዕለቱ የተያዙ አጀንዳዎችን በማጽደቅ ውይይቱን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
በጉባኤው ያጸደቃቸውን ሌሎች አጀንዳዎች በዝርዝር ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽ/ቤት የኮሙኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ተረፈ በዳዳ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ ሥርዓት በትናንትናው ዕለት መካሄዱ ይታወሳል፡፡