Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኮንስትራክሽን ቁጥጥር መረጃ ሥርዓት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ግልፅነትና ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚያስችል የኮንስትራክሽን ቁጥጥር መረጃ ሥርዓት ይፋ ሆኗል፡፡

የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር በቅርቡ ይፋ አድርጎ ወደ ተግባር የገባውን ሀገራዊ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን ኢኒሼቲቭ መሠረት አድርጎ ነው ሥርዓቱ የለማው።

ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ የኮንስትራክሽን ቁጥጥር መረጃ ሥርዓት በዘርፉ የምንሰጠውን አገልግሎት በጥራት ለመስጠትና የቁጥጥር ስራዎችን ለማዘመን አይነተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መስፍን ነገዎ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ደህንነቱ የተጠበቀ የመረጃ ሥርዓት እንዲኖር የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል።

ሥርዓቱ በዋናነት በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ኮንስትትራክሽን ባለስልጣንና በኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በጋራ መልማቱ ተመላክቷል።

የኮንስትራክሽን ቁጥጥር መረጃ ሥርዓት በኮንስትራክሽን ዘርፍ ውስጥ ያሉ ከ26 ሺህ የሚልቁ ተቋማትንና ተዋናዮችን ያቀፈ ሲሆን÷ ግልፅነትና ተጠያቂነትን ለማስፈን እንደሚረዳ ተጠቁሟል፡፡

የኮንስትራክሽን ዘርፉ በጂዲፒው ላይ ያለውን እስከ 20 በመቶ የደረሰ አበርክቶ ወደ 24 በመቶ ማሳደግ የሚያስችል እንደሆነም ተገልጿል።

በዓለምሰገድ አሳዬ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version