አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያን ብልፅግና እውን ለማድረግ የሚያስችል መሰረት እየተጣለ ነው አሉ የብልፅግና ፓርቲ የፌዴራል ተቋማት አስተባባሪ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር )፡፡
የኢኮኖሚ ብልፅግና ክላስተር የ2017 በጀት ዓመት የፖለቲካ እና አደረጃጀት ስራዎች አፈጻጸም የወረዳዎች እውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡
ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ዓመቱ የኢትየጵያን ኢኮኖሚ ወደ ወሳኝ ምዕራፍ የሚያሸጋግር መሰረት የተጣለበት ነው፡፡
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የተበሰረበት መሆኑን አውስተዋል።
ኢትዮጵያ የከርሰ ምድር ሃብቷን አውጥታ ለመጠቀም የሚያስችሏትን ግዙፍ ፕሮጀክቶች ይፋ ማድረጓን ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያ በወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንደምትገኝ አብራርተዋል።
የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ የሚያስችል መሰረት እየተጣለ ነው ሲሉ ማስረዳታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ብልፅግናን እውን ለማድረግ በሚደረገው እንቅስቃሴ የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን ለማለፍ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
ከህዝቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን በአግባቡ ለመመለስ የተጀመሩ የአገልግሎት አሰጣጥ ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የኢኮኖሚና ክላስተር ሰብሳቢ አቶ መላኩ አለበል በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት ለመሆን ያስቀመጠችው ግብ በትክክለኛ መስመር ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
የተፈጥሮ ጋዝ፣ የማዳበሪያ ፋብሪካ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) ይፋ የተደረጉ ፕሮጀክቶች ለዚህ ማሳያዎች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!