Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለታክስ ህግ ተገዢ ሕብረተሰብ ለመፍጠር ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር ይገባል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ ለታክስ ህግ ተገዢ ሕብረተሰብ ለመፍጠር ቅንጅታዊ አሰራረን ማጠናከር ይገባል አሉ የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ።

ሚኒስቴሩ ሀገራዊ የገቢ ዘርፍና ቁልፍ የፌዴራል፣ የክልልና የከተማ አስተዳደር ባለድርሻ አካላት ጋር ሀገራዊ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ኢትዮጵያ እያደገ የመጣ ኢኮኖሚ እየገነባች ብትሆንም ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ ከመሰብሰብ አንፃር ቀሪ ስራዎች አሉ።

ባለፉት የለውጥ ዓመታት የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱን ለማዘመንና ለግብር ከፋዩ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ለታክስ ህግ ተገዢ ሕብረተሰብ ለመፍጠርና የገቢ ሪፎርም ስራን ለማጠናከር የበለጠ መስራት እንደሚያስፈልግና የገቢ ተቋማት በህገወጥ ንግድ ላይ ክትትል በማድረግና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ግብር ከፋዮች ወደ ህጋዊ አሰራር እንዲገቡ ማድረግ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ፍትሃዊ የታክስ አስተዳደር ስርዓት ለመዘርጋት፣ የታክስ አወሳሰንና ሌሎች ስራዎችን ለማሻሻል የግንኙነት ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል ይገባል ብለዋል።

የግብር ከፋዮች የታክስ አከፋፈል እየተሻሻለ ቢሆንም አሁንም የታክስ ስወራና ሌሎች ህገወጥ ስራዎች ስላሉ ብልሹ አሰራርን በመታገል የገቢ ዘርፍን በውጤታማነት መምራት እንደሚገባ አመላክተዋል።

የታክስ አስተዳደርን ዲጂታላይዝ በማድረግ እስከታችኛው መዋቅር ማድረስ፣ የሰው ኃይልና ተቋም ግንባታን በወጥነት ማጠናከር እንደሚገባ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version