አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) እስራኤል እና ሃማስ ለተኩስ አቁም መንገድ ከፋች ነው የተባለለት የመጀመሪያ ምዕራፍ የጋዛ የሰላም እቅድ ላይ ተስማምተዋል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ እስራኤል እና ሃማስ በመጀመሪያው ምዕራፍ የጋዛ የሰላም እቅድ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተናግረዋል፡፡
ስምምነቱ የሁሉንም ታጋቾች መለቀቅና የእስራኤል ወታደሮች በተስማሙበት አካባቢ መውጣትን እንደሚያካትት ጠቅሰዋል፡፡
በቀጣናው ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ስምምነቱ በር ከፋች ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ ÷ ሁለቱም ወገኖች ፍትሃዊና አካታች በሆነ መንገድ እንደሚስተናገዱ አስገንዝበዋል፡፡
ስምምነቱ ታሪካዊ መሆኑን ጠቁመው÷ ለዚህም የኳታር፣ ግብፅና ቱርክ ተወካዮች ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በበኩላቸው÷ ስምምነቱን ለማጽደቅ እና ታጋቾችን ለመመለስ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
“ለእስራኤል ታላቅ ቀን” ሲሉ ስምምነቱን ያወደሱት ኔታንያሁ÷ የእስራኤል ወታደሮች እና የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ታጋቾችን ለማስለቀቅ ላደረጉት ጥረት ምስጋና ችረዋል፡፡
የእስራኤል ካቢኔ በስምምነቱ ላይ ድምጽ የሚሰጥ ሲሆን÷ ተቀባይነት ካገኘ የእስራኤል ጦር በ24 ሰዓት ውስጥ ወደ ተስማማበት አካባቢ የሚመለስ ሲሆን÷ ታጋቾች ደግሞ በ72 ሰዓታት የጊዜ ገደብ ውስጥ እንደሚለቀቁ ተመላክቷል፡፡
ሃማስ በበኩሉ÷ በጋዛ ያለውን ጦርነት ለማስቆም ስምምነት ላይ መደረሱን አረጋግጦ አሜሪካና የሚመለከታቸው ሀገራት እስራኤል የስምምነቱን ውሎች ሙሉ በሙሉ መተግበሯን እንዲያረጋግጡ ጠይቋል።
ስምምነቱ በጋዛ ላይ የሚደረገውን ጦርነት የሚያስቆም፣ ሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲገባ የሚፈቅድ እንዲሁም የታጋቾችንና እስረኞችን መለቀቅ ተግባራዊ የሚያደርግ እንደሆነ መግለጹንም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በዮናስ ጌትነት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!