አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ማናቸውም አይነት ተሽከርካሪዎች ከቀረጥ ነጻ ሆነው ወደ ሀገር እንዲገቡ ተወስኗል አለ የገንዘብ ሚኒስቴር፡፡
ሚኒስቴሩ ለፋና ዲጂታል እንዳስታወቀው ÷ ኢትዮጵያ ከፍተኛ መጠን ያለው የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ያላት መሆኑ ቢታወቅም ለዘመናት የዚህ የተፈጥሮ ሃብት ተጠቃሚ ሳትሆን ቆይታለች፡፡
ይህንን ሁኔታ ለመለወጥ መንግስት ሲያደርግ የቆየው እልህ አስጨራሽ ጥረት ተሳክቶ በቅርቡ በካሉብ አካባቢ የሚገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችል ኢንዱስትሪ ተመርቆ የተፈጥሮ ጋዝ የማምረት ስራ በይፋ ተጀምሯል።
ይህን ምርት ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ ቤንዚን እና ናፍታ የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎችን የተፈጥሮ ጋዝ በሚጠቀሙት ተሽከርካሪዎች መተካት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥቷል፡፡
የተፈጥሮ ጋዝ የሚያመነጨው በካይ አየር እጅግ በጣም ዝቅተኛ የሆነ፣ ለተለያየ የሀይል ምንጭ አገልግሎት ሊውል የሚችል፣ በሀይል አጠቃቀም ረገድ ውጤታማነት እንዳለው የገለጸው ሚኒስቴሩ፤ የተፈጥሮ ጋዝ በኢትዮጵያ የሚመረት በመሆኑ ለነዳጅ ግዥ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሪ ያስቀራል።
በመሆኑ መንግስት የተፈጥሮ ጋዝ አጠቃቀምን ለማበረታታት ይህ መመሪያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ማናቸውም አይነት የደረቅ፣ የፈሳሽ ጭነት እና የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ከጉምሩክ ቀረጥ ነጻ ሆነው ወደ ሀገር እንዲገቡ መፈቀዱን አስታውቋል፡፡
ይህ መመሪያ ከወጣበት ቀን በፊት ወደ ሀገር እንዲገቡ ከተፈቀደላቸው እንዲሁም በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገር ከሚገቡት በስተቀር በቤንዚን እና ናፍታ የሚሰሩ የጭነትና የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር እንዳይገቡ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግም አሳስቧል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!