አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2017/18 ምርት ዘመን የመኸር ወቅት 289 ሺህ 300 ሄክታር መሬት በቅባት እህል ተሸፍኗል።
የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ኸሊፋ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፤ በምርት ዘመኑ የመኸር ወቅት 1 ነጥብ 56 ሚሊየን ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች ተሸፍኖ በጥሩ ቁመና ላይ ይገኛል።
በዘር ከተሸፈነው ሰብል ውስጥ 289 ሺህ 300 ሄክታር መሬት በቅባት እህል የተሸፈነ መሆኑን ገልጸው፤ 177 ሺህ 149 ሄክታር በሰሊጥ፣ 124 ሺህ 538 ሄክታር በአኩሪ አተር 81 ሺህ 470 ሄክታር በለውዝ መሸፈናቸውን ተናግረዋል።
በክልሉ የቅባት እህሎች በስፋት እንደሚመረቱ ጠቅሰው፤ በክልሉ የሰፈነው ሰላም ወረዳዎች በተረጋጋ ሁኔታ ወደ እርሻ መግባት በመቻላቸው ከዕቅድ በላይ ማሳካት መቻሉን ገልጸዋል።
የቅባት እህል ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት መሰጠቱን የተናገሩት አቶ ባበክር፤ የውጭ ምንዛሬ በማምጣት ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት አስተዋጽኦ የሚያበረክተውን የቅባት እህል ውጤታማ ለማድረግ በአብዛኛው በኩታገጠም ዘዴ መዘራቱን አስረድተዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!