አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ (ኢባትሎ) የመርከብ አዛዥ ሰልጣኞችን አስመርቋል።
የባቦጋያ ማሪታይም ሎጂስቲክስ አካዳሚ ከሚያዝያ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሲያሰለጥናቸው የቆየው 18 ሰልጣኞችን ነው በዛሬው ዕለት ያስመረቀው።
የኢባትሎ ዋና ሥራ አስፈፃሚ በሪሶ አመሎ (ዶ/ር) በሥነ ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዘርፉን ለማሳደግ ተጨማሪ መሰል ስልጠናዎችን በቀጣይ በስፋት ለመስጠት ይሰራል ብለዋል።
በዘርፉ በዓለም አቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ ለመሆን በርካራ ስራዎች እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል።
ኢትዮጵያ በአሁን ወቅት የባህር በር መዳረሻ ባይኖራትም ቁርጠኝነታችን እና ዝግጅታችን ወደ ባህሩ ለመመለስ የምናደርገውን ጉዞ በእናንተ በተመራቂዎች ውስጥ እናያለን ብለዋል።
የባቦጋያ ማሪታይም አካዳሚ ዲን አቶ ሲራጅ አብዱላሂ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ በአሁኑ ወቅት መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።
በዘርፉ ኢትዮጵያ እያበረከተች ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑንም አብራርተዋል።
መርከበኞቻችን በመላው ዓለም በተጓዙበት ሁሉ ስራቸውን በአግባቡ በመወጣት የኢትዮጵያን መልካም ገፅታ ይገነባሉ ነው ያሉት።
አካዳሚው ከዓለም አቀፍ የመርከብ ኩባንያዎች፣ ከማሪታይም ማሰልጠኛ ተቋማት እና ከሎጂስቲክስ ኩባንያዎች ጋር ትስስሩን እያጠናከረ እንደሚገኝ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል።
ኢባትሎ ሀገራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሆነ ገልጸው፤ ለኢትዮጵያ ልማትና ዕድገት የኋላ ደጀንነቱን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል ነው ያሉት።
በወንድማገኝ ጸጋዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!