Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ጥራትና ተደራሽነት በትኩረት እየተሰራ ነው – ከንቲባ ከድር ጁሃር

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለትምህርት ጥራትና ተደራሽነት በትኩረት እየተሰራ ይገኛል አሉ የከተማዋ ከንቲባ ከድር ጁሃር።

በከተማ አስተዳደሩ በ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል።

በዚህም መሰረት በከተማ አስተዳደሩ 574 በማምጣት ከፍተኛውን ውጤት ላስመዘገበችው ተማሪ አፎሚያ ጋሹ ከ250 ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ የኤሌክትሮኒክስ ቁሶችና 45 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶለታል።

ከንቲባ ከድር ጁሃር በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ በ2017 የትምህርት ዘመን ለተመዘገበው የተሻለ ውጤት የመምህራንና የወላጆች ድጋፍና ክትትል እንዲሁም በዘርፉ የተሰሩ የለውጥ ስራዎች ማሳያ ናቸው።

አስተዳደሩ ለትምህርት ጥራትና ተደራሽነት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው፥ ወላጆች ከመምህራንና ትምህርት ቤቶች ጋር የጀመሩትን የድጋፍና ክትትል ስራዎች በማጠናከር የተሻለ ውጤት እንዲመጣ መትጋት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

ተሸላሚ ተማሪዎች በቀጣይም ትምህርታቸውን በትጋት በመከታተልና ውጤታማ በመሆን ሃገርን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ መስራት እንዳለባቸው ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version