Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአዳብና በዓል በአዲስ አበባ ከተማ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዳብና በዓል በአዲስ አበባ ከተማ በወዳጅነት ፓርክ የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት እየተከበረ ነው፡፡

አዳብና በጉራጌ ማሕበረሰብ ዘንድ ከመስከረም 16 እስከ ጥቅምት አምስት ቀን ድረስ ወጣቶች በተለያዩ ባሕላዊ ትውፊቶች የሚያከብሩት በዓል ነው።

የማሕበረሰቡ ባህላዊ መገለጫ ከሆኑት ባህልና እሴቶች መካከል አንዱ የሆነው አዳብና የመተጫጫ፣ የነፃነት እንዲሁም የተጠፋፉ ወዳጆች የሚገናኙበት በዓል መሆኑም ተመላክቷል።

በአከባበር ሥነ ሥርዓቱ ላይ በሀገርና ዓለም አቀፍ ደረጃ ባሕልን በማስተዋወቅ የቱሪስት ስበት እንዲሆን መሰል ፌስቲቫሎች ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተጠቅሷል፡፡

በመላኩ ገድፍ

Exit mobile version