Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ዶናልድ ትራምፕ እስራኤል ቴል አቪቭ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በእስራኤል እና ሀማስ መካከል ከተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት በኋላ ወደ ቴል አቪቭ አቅንተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ቴል አቪቭ ቤን ጎሪዮን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በወታደራዊ ትርኢቶች አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

ትራምፕ በቆይታቸው የተኩስ አቁም ስምምነቱን ተግባራዊነት እንደሚገመግሙና ቀሪ የእስራኤል ታጋቾች መለቀቅን በተመለከተ ከእስራኤል ክኔሴት ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በአሜሪካ አሸማጋይት የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነቱ ተግባራዊ መደረግ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ በጋዛ ጦርነት የቆመ ሲሆን÷ እስራኤል ከአብዛኛው የጋዛ ክፍል ጦሯን አስወጥታለች፡፡

በተመሳሳይ ስምምነቱን ተከትሎ ሀማስ የእስራኤል ታጋቾችን መልቀቅ እንደጀመረና በዛሬው ዕለት 7 የእስራኤል ታጋቾችን ለቀይ መስቀል እንዳስረከበ ስፑትኒክ ኒውስ ዘግቧል፡፡

በሚኪያስ አየለ

Exit mobile version